አዝ፦ በኩርነትህን ለምን ሸጥከው ኢየሱስን ለምን ለወጥከው ክብርና ገንዘብ ጠፊ ነው የማይጠፋውን ምረጠው ጌታ ይሻልሃል ለዘለዓለም ሕይወት የሆነህ (2x) ለማያጠግብህ እሮጠህ ምናምንቴ ነገር ወደህ ረብ ረድኤት በማይሆነው በኩረነትህን ሸጥከው አዝ፦ በኩርነትህን ለምን ሸጥከው ኢየሱስን ለምን ለወጥከው ክብርና ገንዘብ ጠፊ ነው የማይጠፋውን ምረጠው ጌታ ይሻልሃል ለዘለዓለም ሕይወት የሆነህ (2x) ብዙዎች ወደቁ ተጠልፈው በገንዘብ ፍቅር ተነድፈው ብልጽግና ያታልላል ይሁዳ ጌታውን ሽጧል አዝ፦ በኩርነትህን ለምን ሸጥከው ኢየሱስን ለምን ለወጥከው ክብርና ገንዘብ ጠፊ ነው የማይጠፋውን ምረጠው ጌታ ይሻልሃል ለዘለዓለም ሕይወት የሆነህ (2x) ሰይፍ ከዋጠዉ የበለጠ የኃጢአት ዱር ብዙ ዋጠ አንተን የዋጠህ ምንድን ነው ነፍስህን አንቆ የያዘው አዝ፦ በኩርነትህን ለምን ሸጥከው ኢየሱስን ለምን ለወጥከው ክብርና ገንዘብ ጠፊ ነው የማይጠፋውን ምረጠው ጌታ ይሻልሃል ለዘለዓለም ሕይወት የሆነህ (2x)