Song Lyrics

ከዚህም የሚበልጥ

አዝ፦ ከዚህም የሚበልጥ የጌታ ኃይል ሲገለጥ እናያለን ገና የክብሩን ደመና ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና ጌታ በመንፈሱ በቅሉ መርምሮ ሥራችንን ሁሉ ቢነግረን ዘርዝሮ በዕውቀቱ ተደንቀን በኑሮአችን አፍረን ንስሐ ገብተናል ይቅር በለን ብለን አዝ፦ ከዚህም የሚበልጥ የጌታ ኃይል ሲገለጥ እናያለን ገና የክብሩን ደመና ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና ኃጢአታችንን በደሙ አነጻው የእኛ ጌታ ኢየሱስ ይቅርታው ብዙ ነው ርኩስ መናፍስትን በኃይሉ ያስወጣል በወንጌሉ ሥልጣን መንግሥቱን ያሰፋል አዝ፦ ከዚህም የሚበልጥ የጌታ ኃይል ሲገለጥ እናያለን ገና የክብሩን ደመና ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና ጌታ ሆይ! እያለ ለሚቃትተው ማዳኑ ሊመጣ ጽድቁ ሊገለጥ ነው የእግዚአብሔር ምሕረት ሁሉንም አብስሩ የበረከት ዝናብ ይኸው ውሽንፍሩ አዝ፦ ከዚህም የሚበልጥ የጌታ ኃይል ሲገለጥ እናያለን ገና የክብሩን ደመና ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና ረሃብተኛ ሲመገብ ልኡል ቃሉን ሲሰጥ በጻድቅን ዕልልታ ምድር ስትናወጥ በምሥጋና ዜማ በደስታ ዝማሬ በታላቁ መከር የአገልግሎት ፍሬ አዝ፦ ከዚህም የሚበልጥ የጌታ ኃይል ሲገለጥ እናያለን ገና የክብሩን ደመና ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection