አዝ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬ እስከ ለዘለዓለም ያው ነህ (3x) ሰማያት አርጅተው ከምድር ጋር ሲያልፉ በውስጣቸው ያሉት ኃይላትም ሲጠፉ አንተ ግን አቤቱ ለዘለዓለም ያው ነህ መለወጥ ሳያሻህ ደምቀህ ትኖራለህ አዝ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬ እስከ ለዘለዓለም ያው ነህ (3x) እኛ የምናመልከው ሳይታክት ሳይደክም በሥልጣኑ ገኖ ይኖራል ዘለዓለም አልፋ ነው ኢየሱስ ዖሜጋም ነው ጌታ በበረቱብን ላይ ክንዱ የበረታ ሃሌ ሉያ! ሃሌ ሉያ! ሃሌ ሉያ! ተጠብቀናል ታማኝ በሆነው ኢየሱስ በአንተ ጉያ ገና ኃጢአተኞች በደለኞች ሳለን የእግዚአብሔርን ፍቅር በክርስቶስ አየን በመስቀል ላይ ሞቱ የእኛን መርገም ወስዶ ጽድቁን አልብሶናል ማቃችንን ቀዶ አዝ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬ እስከ ለዘለዓለም ያው ነህ (3x) በእኛ ላይ ያለው ከጥንትም ያሰብከው ዛሬም እንዳየነው ዓላማህ ፍቅር ነው በክንፎችህ ጥላ ኖረናል ተማምነን በድል እንዘልቃለን በእጆችህ ተይዘን ሃሌ ሉያ ! ሃሌ ሉያ ! ሃሌ ሉያ ! ተጠብቀናል ታማኝ በሆነው ኢየሱስ በአንተ ጉያ