አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ በደልን የምቆጥር ነኝ ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ ትንቢትና ዕውቀት መገለጥ ቢኖረኝ ተራራን የሚያፈርስ ዕምነት ሁሉ ባገኝ በሰዎች በመላዕክት ልሳን ብናገርም ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ በደልን የምቆጥር ነኝ ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ ፍቅር ይታገሳል ቸርነት ያደርጋል በዕውነት ደስ ይለዋል ዓመጽን ይጠላል አይቀናም አይመካም ራሱን ያዋርዳል እየተበደለ ሁሉን ይቅር ይላል አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ በደልን የምቆጥር ነኝ ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ በአመቺ ቦታ ላይ ጠላቱን አግኝቶ በመልካሙመንገድ በፍቅር ሸኝቶ በሰላም የሚሰድ ከሰው ልጆች ማነው? ዳዊት በዘመኑ ይህን አደረገው አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ በደልን የምቆጥር ነኝ ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ ጠላቶችህ ሳለን ሞትህ ካስታረቀን በመስቀል ላይ ፍቅርህ ሕይወት ከሰጠኸን ሕይወት እንድናተርፍ ሰውን ሁሉ ወድደን በዕውነተኛው ፍቅር ጌታ አጥለቅልቀን አዝ፦ ፍቅር ፍቅር ፍቅር ነው የጐደለኝ በደልን የምቆጥር ነኝ ጌታ ይቅር ባይ አድርገኝ መራራ ሥሬን ቁረጥልኝ በአንተው ፍቅር የጣፈጠ ሕይወት ስጠኝ