Song Lyrics

የጠፋውን ማን ይፈልጋል

አዝ፦ የጠፋውን ማን ይፈልጋል? የተጐዳውን ማን ያክማል? ሰባራውን ማን ይጠግናል? የፈረሰውን ማን ያድሳል? ቤቱ ፈርሶ እያየህ የእግዚአብሔር የራስህን ኑሮ ልታሳምር ያለጌታ ልትከብር ሮጠሃል እስከዛሬ ውስጡ ግን ባዶ ነው የጨበጥከው ፍሬ አዝ፦ የጠፋውን ማን ይፈልጋል? የተጐዳውን ማን ያክማል? ሰባራውን ማን ይጠግናል? የፈረሰውን ማን ያድሳል? በጐዱ ለአራዊት መብል ሆኑ እረኛ በማጣት ተበተኑ ራስህን ስታሰማራ ለምቾትህ ስትሠራ ይታይህ ወዳጄ የመንጋው መከራ አዝ፦ የጠፋውን ማን ይፈልጋል? የተጐዳውን ማን ያክማል? ሰባራውን ማን ይጠግናል? የፈረሰውን ማን ያድሳል? መክሊትህ ወዴት ነው? ወንድሜ ሆይ! እንደ ሃኬተኛው ቀበርከው ወይ? የሰጠህ ይጠይቅሃል! አደራውን የት አድርገሃል? የምትጠፋውን ነፍስ ከእጅህ ይፈልጋል አዝ፦ የጠፋውን ማን ይፈልጋል? የተጐዳውን ማን ያክማል? ሰባራውን ማን ይጠግናል? የፈረሰውን ማን ያድሳል? ነፍስን ሊሰበስብ የተጠራ ለጠፉት የሚያዝን የሚራራ የምሥራች የሚያወራ በፍጻሜው ይሸለማል ዘለዓለም ይደምቃል እንደ ሰማይ ጸዳል አዝ፦ የጠፋውን ማን ይፈልጋል? የተጐዳውን ማን ያክማል? ሰባራውን ማን ይጠግናል? የፈረሰውን ማን ያድሳል?
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection