Song Lyrics

ማደሪያዎችህ

አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ ክቡር ድንጋዮች ሕያዋን ልጆች በበጉ ደም የተዋጁ ሰዎች ቤተ መቅደስ ለመሆን ታነጹ ማደሪያ ሆኑለት ለንጉሡ አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ በዓለም አዕላፍ ዕርካታን ያጡ ዝናህን ሰምተው ከሩቅ የመጡ በኃጥአን ድንኳን ከሚቀመጡ በአንተ ማደሪያ መጣል መረጡ አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ በጓዳዎችህ ክቡር ነገሮች ተከምረዋል የሰማይ ሃብቶች በመብራት በዘይትህም ቅባቶች እጅግ ደመቁ የአንተ ልጆች አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ ካህናቶችህ በመለከቶች መዘምራን በዜማ ዕቃዎች ባንድነት ቃና ወጣ ድምጻቸው ከፍ አደረጉህ በምሥጋናቸው አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ በዘለዓለማዊው ምሕረቱ ልኡል ጐበኘን በቸርነቱ ጌታ ለሕዝቡ ሰጠ ሞገሱን የአምላኬ ክብር ሞላ መቅደሱን አዝ፦ ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ ስግደት ይቅረብልህ ስግደት ይቅረብልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection