Song Lyrics

የፀሎት ቤት ይሁን

አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x) በልጅህ ደም ሕይወት ሰላም ይሁን! ብለህ ለሐጢአታችን ይቅርታን አውጀህ እግዚአብሔር ሆይ! ታረቅኸን ተመስገን የክብርህ ማረፊያ መቅደስህ አደረግኸን (2x) አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x) ዙፋንህ በሰማይ የሆነ ንጉሥ በምድር በእኛ መሃል ስምህ ይቀደስ የመዓዛ ሽታ መሥዋዕታችንን ምሥጋናን ተቀበል ከሕይወታችን (2x) አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x) ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያሉ መላዕክት በትጋት ሲያመልኩህ ቀንም ሆነ ሌሊት ከእኛም ይድረስህ ውዳሴ ማሕሌት ምልጃም ጸሎታችን ምሥጋና ስግደት (2x) አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x) መቅረዝህም ይንደድ ይታይ ብርሃንህ የጸሎት ቤትህን ሙላው በክብርህ አሕዛብም ይምጡ ወደ ጸዳልህ ይስገዱልህ ድነው በቅዱስ ስምህ (2x) አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x) የዓለም ገበያ እንዳይሆን ማትረፊያ ቀድሰህ ጠብቀው የአንተን ማደሪያ የዘለዓለም ሕይወት ፈውስን መቀበያ ይሁንልን ቤትህ የመንፈስ መኖሪያ (2x) አዝ፦ የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection