Song Lyrics

ባለፍኩበት መንገድ

አዝ፦ ባለፍኩበት መንገድ ለእኔ ተጠንቅቆ እዚህ ያደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ ሃገሬ እገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ (2x) ማዕበሉ ሳይጥለኝ ውኃ ሳያሰጥመኝ እጄን በእጁ ይዞ ወንዝ አሻገረኝ የፈተናው እሣት ወላፈን ሳይጐዳኝ በጌታዬ ፀጋ በሕይወት አለፍኩኝ አዝ፦ ባለፍኩበት መንገድ ለእኔ ተጠንቅቆ እዚህ ያደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ ሃገሬ እገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ (2x) ከሕያዋን ጋራ ኖሬ እንዳከብርህ ፈተናን አልፌ እንዳመሰግንህ ኢየሱስ ከጐኔ ቆሞ አበረታኝ ከአንበሣው አፍም ደጋግሞ አወጣኝ አዝ፦ ባለፍኩበት መንገድ ለእኔ ተጠንቅቆ እዚህ ያደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ ሃገሬ እገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ (2x) ሕይወቴን ለአምላኬ አደራ እየሰጠሁ በእረኝነቱ ሥር ሳልሰጋ እኖራለሁ ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ በእርሱ ተጠብቄ አገሬ እገባለሁ አዝ፦ ባለፍኩበት መንገድ ለእኔ ተጠንቅቆ እዚህ ያደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ ሃገሬ እገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ (2x) ጌታ የሠራውን ድንቅ አስታውሳለሁ ስላለፈው ዘመን አመሰግናለሁ ከፊቴ ላለውም በእርሱ እደገፋለሁ በዘለዓለም ክንዱ በእቅፉ እኖራለሁ አዝ፦ ባለፍኩበት መንገድ ለእኔ ተጠንቅቆ እዚህ ያደረሰኝ ከክፉ ጠብቆ እስከ ፍጻሜውም ያቆመኛል ጌታ ሃገሬ እገባለሁ እምነቴ ሳይፈታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection