አቤቱ ጌታችን! እስኪ እናመስግንህ ለውለታህ ምላሽ ክበር እንበልህ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥረን ሽቶ ዕምነት ተስፋችንን ሊያጨልም ዝቶ አምርሮ ቢነሣም እጅግ ተቆጥቶ ተገዝቶ አየነው በአንተ ድል ተነሥቶ ስለ ዕምነታችን ስለ ሕይወታችን የተሟገትክልን ተመስገን ጌታችን የተጓዝንበትን መንገድ ሲያቋርጥ ጠላታችን አልፎ ዕንቅፋት ቢያስቀምጥ የተመሸገውን ከፍ ያለውን ቅጥሩን አፈራርሰህ ጣልከው ኢየሱስ ተመስገን አንተ ቅን የሆንህ መንገድ ታቀናለህ የተዘጋውንም በር ትከፍትልናለህ የሕዝብህን ስድብ ከምድር አስወግደህ ከፊታቸውም ላይ እንባቸውን አብሰህ ራሣቸውን በዘይት በሞገስ ቀብተህ በምሥጋናቸውም አንተ ትነግሣለህ ለታናሹ መንጋ በዝቷል ቸርነትህ ክበር አምላካችን ዘለዓለም ልዕኡል ነህ ግብዣን አዘጋጅተህ በክብር ጠራኸን በንጉሥ ገበታ ይኸው አስቀመጥኸን በክርስቶስ ኢየሱስ በከበረው ሥፍራ ነፍሣችን ጠገበች ከሕይወት እንጀራ ፈቅደን ከልባችን እናመልክሃለን ለዘለዓለሙም ለአንተ እንገዛለን