Song Lyrics

ቃሉን ከቶ የማያጥፍ

አዝ፦ ቃሉን ከቶ የማያጥፍ ታማኝ አምላክ ነውና የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና የኃጢአትን ከተማ የዲያብሎስን ሥራ ሲያፈራርሰው አይተናል ያን ምሽግ ያንን ተራራ ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ የሕይወታችን ብርሃን የተስፋ ቃሉን ፈጸመው በሞቱ እኛን በማዳን አዝ፦ ቃሉን ከቶ የማያጥፍ ታማኝ አምላክ ነውና የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና በሰላምና በሕይወት በበጐ ነገርም ምክር አበሳችን እንዲወገድ እሮሮአችንም እንዲቀር በእኛ ያለውን ነገር ጌታ እግዚአብሔር አይቶ ቀንበራችንን ሰበረው ለቅሶአችንን እርሱ ሰምቶ አዝ፦ ቃሉን ከቶ የማያጥፍ ታማኝ አምላክ ነውና የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና የሲኦልን ማስፈራራት የመከራን አውሎ ነፋስ የኃያላኑን ጭካኔ የቁጣቸውን እስትንፋስ የማዕበሉን ሁሉ ጩኸት የዓመጽንም ዝማሬ በሥልጣኑ ቃል ገስጾ ዝም አሰኝቶታል ዛሬ አዝ፦ ቃሉን ከቶ የማያጥፍ ታማኝ አምላክ ነውና የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና የመማጸኛ ግንብ ነው የድሆች ሁሉ መጠጊያ ምቹ መሸሸጊያ ዓለት የለንም ከኢየሱስ ወዲያ ብዙዎቹም ይድናሉ ገብተው ከዚህ መጠለያ ስለሚሆንልን ሁሉ ይክበር ጌታ ሃሌሉያ! አዝ፦ ቃሉን ከቶ የማያጥፍ ታማኝ አምላክ ነውና የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection