Song Lyrics

ቤዛ የሆንክልኝ

አዝ፦ ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x) በወርቅ ይሁን በብር በጥበብ በዕውቀት የዳነ ማን አለ ከኃጢአት ውድቀት? ጌታ ሆይ ! አንተ ነህ ጽድቅን ያለበስኸኝ በምሕረት አማልደህ ከዓብ ያስታረቅኸኝ (2x) አዝ፦ ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x) በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ ከዘለዓለም ሞት ዳንኩኝ ከመከራ በነጻ ታድዬ የጽድቅን ሥጦታ ምሥጋና እሰዋለሁ ለተቤዠኝ ጌታ (2x) አዝ፦ ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x) ብላቴንነቴን ድካሜን ገምተህ አንተ ብርቱ ጌታ በእኔ ላይ ተገልጠህ የበረታብኝን ጠላቴን ቀጥቅጠህ ድል ያጐናተጸፍኸኝ ኢየሱስ አንተ ነህ (2x) አዝ፦ ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x) መልካሙን ሥራህን በሕይወቴ ፈጽመህ እንድትታይብኝ በኑሮዬ ጐልተህ ይህ ነው ልመናዬ የዘወትር ጸሎቴ ክብሬ ዕርካታዬ አንተ ነህ ትምክህቴ (2x) አዝ፦ ቤዛ የሆንክልኝ ጌታዬ የሕይወቴ መልሕቅ ድጋፍ የዕርምጃዬ ማዳንህ ተገልጾ አይቻለሁ ጽድቅህን ስለዚህ በደስታ ላመስግን ስምህን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection