አዝ፦ የኃጢአተኛውን ጥፋት እግዚአብሔር መቼ ይወዳል? የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል በምክሩ ያስባል ምሕረትና ዕውነት ፍቅርና ቸርነት የሞላው ጌታ ኃጥዕ በንስሐ ይቀበል ይቅርታ ማንም እንዳይጠፋ መድህን ሞቶልናል ክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛ ሆኖልናል አዝ፦ የኃጢአተኛውን ጥፋት እግዚአብሔር መቼ ይወዳል? የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል በምክሩ ያስባል ሰው ግን በውድቀቱ ለምን ተስፋውን ይቆርጣል ቶሎ? ለምን ይቀናዋል መውረድ አሽቆልቁሎ? ጌታን እጠብቃለሁ ቢገድለኝም ብሎ በዕምነት የሚቆም አይቀርም ጐስቁሎ አዝ፦ የኃጢአተኛውን ጥፋት እግዚአብሔር መቼ ይወዳል? የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል በምክሩ ያስባል የሚወደውን ልጅ እግዚአብሔር ለጥቅሙ ይቀጣዋል መክሮ ይገስጸዋል ያስተካክለዋል በአባትነት ዓይኑ ይመለከተዋል ሲፍገመገም ቢያየው ፍጥኖ ይደግፈዋል አዝ፦ የኃጢአተኛውን ጥፋት እግዚአብሔር መቼ ይወዳል? የተጣለ ሰው እንኳን ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል በምክሩ ያስባል