Song Lyrics

እኛ ግን የሞተልንን

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
አይሁድ ምልክት ይለምናሉ ግሪኮች ጥበብ ይሻሉ ጌታን ጥለውይቅበዘበዛሉ አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን በደሙም የተቤዥንን አዳኝነቱን ንጉሥነቱን ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን አዎን እንሰብካለን (2x) ያልገባቸው ያላወቁት በድንቅ እንደ ሞኝነት ቢቆጥሩትም በመስቀሉ ቃል አናፍርበትም አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን በደሙም የተቤዥንን አዳኝነቱን ንጉሥነቱን ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን አዎን እንሰብካለን (2x) የመዳኑን ፀጋ መጠራቱን ከኃጢአን መሃል መውጣቱን ባይቀበሉትም እንኳን ወንጌሉን አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን በደሙም የተቤዥንን አዳኝነቱን ንጉሥነቱን ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን አዎን እንሰብካለን (2x) ለእኛ ነህ መከታችን ኢየሱስ ከለላችንም ክርስቶስ አለቃችንም ነው የሰላም ንጉሥ አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን በደሙም የተቤዥንን አዳኝነቱን ንጉሥነቱን ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን አዎን እንሰብካለን (2x) ባዶ ተስፋ ፍፁም አናወራም ከሥጋችን አንዘራም ጌታችን አለና አንፈራም አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን በደሙም የተቤዥንን አዳኝነቱን ንጉሥነቱን ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን አዎን እንሰብካለን (2x) ለሚጠይቀን ሁሉ መልሳችን የቀራንዮ ወዳጃችን ኢየሱስ ጌታ ነው ትምክህታችን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection