Song Lyrics

እኔም ያንን ፀጋ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
የመከራ እቶን የማንጠሪያ እሳት የመፈተኛ ፍም የመመዘኛ ጣት ነበር በጀግኖች ዘንድ ባለፉት ጦረኞች ባለፉበት መንገድ የድል ባለቤቶች አዝ፦ እኔም ያንን ፀጋ በሕይወቴ አድርጌ በችግሬ ሰዓት ጌታዬን ጠብቄ ልደርስ እወዳለሁ ወደዚያ ደረጃ በሚሰጠኝ ጉልበት በእምነት እርምጃ በቀደመው ትውልድ እሳት ነበር ልኩ ለእምነት ትጋዳዮች የትግል መድረኩ ለማይጠፋው ክብር ለሕያውም ተስፋ ተዋግተው አልፈዋል በትልቅ ነቀፋ አዝ፦ እኔም ያንን ፀጋ በሕይወቴ አድርጌ በችግሬ ሰዓት ጌታዬን ጠብቄ ልደርስ እወዳለሁ ወደዚያ ደረጃ በሚሰጠኝ ጉልበት በእምነት እርምጃ አምላካቸው ከብሯል በአምልኮ ስግደት በትልቅ ተጋድሎ በወንጌል ጤንነት ከብረው አስከብረው የሕይወታቸውን ጌታ ሊገናኙት ወጡ ያንን ባለ ውለታ አዝ፦ እኔም ያንን ፀጋ በሕይወቴ አድርጌ በችግሬ ሰዓት ጌታዬን ጠብቄ ልደርስ እወዳለሁ ወደዚያ ደረጃ በሚሰጠኝ ጉልበት በእምነት እርምጃ እኛም ተጠርተናል ልንመልስ እነርሱን የመክራን እሳት እንድናየው ልኩን ስለዚህ ተጋደል የወንጌል አርበኛ ጌታም እንዲጥለው ያንተን ወደረኛ ነውና ድል የእኛ አዝ፦ እኔም ያንን ፀጋ በሕይወቴ አድርጌ በችግሬ ሰዓት ጌታዬን ጠብቄ ልደርስ እወዳለሁ ወደዚያ ደረጃ በሚሰጠኝ ጉልበት በእምነት እርምጃ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection