Song Lyrics

በእምነት እኖራለሁ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
ከምድር በላይ ቢሆን ከሰማይ በታች መግባት መውጣታችሁ ዘወትር ተመልካች እንደ ኢየሱስ ያለ ማንን አገኛችሁ የሕይወት ዋስትና ጌታ የሚሆናችሁ አዝ፦ በእምነት እኖራለሁ ጌታዬን አውቃለሁ የኔን ፅኑ አምባ ተተግኘዋለሁ ወጀቡን ሳልፈራ ታግዬ እወጣለሁ የክብር ሽልማቴን ከእጁ እረከባለሁ ለነገ አይጨንቀኝም ጭጋግ ቢሸፍነው ወይኑ ቢጠወልግ ሃሩሩ ቢያሰጋም ለእግሬ መብራት ነው ቃሉ በእጄ ያለው የተፈጥሮ አዛዥ ኢየሱስ ሕያው ነው አዝ፦ በእምነት እኖራለሁ ጌታዬን አውቃለሁ የኔን ፅኑ አምባ ተተግኘዋለሁ ወጀቡን ሳልፈራ ታግዬ እወጣለሁ የክብር ሽልማቴን ከእጁ እረከባለሁ ፈቃዱ ሲሞላ ጌታዬ ከብሮ ሳይ ምድር ዕልል ስትል ሲያጨበጭብ ሰማይ መጠለያ ልብሴ እንጀራዬ ያ ነው ነፍሴ ትጠግባለች በክብር በግርማህ አዝ፦ በእምነት እኖራለሁ ጌታዬን አውቃለሁ የኔን ፅኑ አምባ ተተግኘዋለሁ ወጀቡን ሳልፈራ ታግዬ እወጣለሁ የክብር ሽልማቴን ከእጁ እረከባለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection