Song Lyrics

መብዛት መዋረዱን

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
አዝ፦ መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (2x) በቃሌ ስበትን በከንፈሬ ተሳስቼ እንዳልጥል ያገኘሁት መስሎኝ እየከነፍኩ ስሮጥ ወደ ክፋት ሰው ሁሉ አስፈርቶኝ ስቅበዘበዝ አግኝቶኝ ያ ጌታ እብድነቴን ገፎት ቤት ሰጠኝ አገኘሁ ይቅርታ አዝ፦ መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (2x) እንደ ሰባ እንቦሳ ስፈነጥዝ በተራራ ሕይወት ተመስገን እያልኩኝ ኢየሱስን በበረከት ምንጮች ከዛም ሳላስበው በመቅሰፍት በሸለቆ ስገኝ ተሰብሬ ሳለቅስ በጨለማ ብርሃን ሆንክልኝ አዝ፦ መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (2x) ሰማያዊ ፀዳል ተገርስሶ የተነሳ ቢመስል ከደብረዘይት መውረድ ልብን ቢያብሰለስል ጌታ አልተለየኝም አብሮኝ አለ በሸለቆ ሕይወት የተራሮች አምላክ ብቻ አይደለም አልሰጠኝም ለሞት አዝ፦ መብዛት መዋረዱን መራቡን መጥገቡን ሁሉን ተምሬያለሁ ተመልክቸዋለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection