Song Lyrics

ኃይልን ቀምሼ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
ኃይልህን ቀምሸ ክንድህን አይቼ ክብርህ ተንሰራፍቶ በዓይኔ ተመልክቼ ያን ሁሉ ዘነጋሁ ዓለምን አይቼ እኔ ግን ተመከርኩ ከአንተ ተለይቼ አንተ ግን ጌታዬ ጠብቀኝ ልጅህን እግሬን ልትመልሰው ልትረዳኝ ፍጠን (2x) ፍቅርህ ግድ ይለኛል እንዳልለይህ ኮብልዬም ብጠፋ ከድሎት ደጅህ ከችጋሩ ሌላ ፀጋ ምህረትህ አያስጨክኑኝም ትዝታዎችህ ከቤትህ ሸሽቼ ወዴት እደርሳለሁ ከመንፈስህ ርቄ ወደማን እሄዳለሁ (2x) ምድሪቱ አንገላታኝ አላማዬን ስቼ ወደ ግራና ቀኝ ዓይኖቼን አንስቸ ኃጥዕ ሲለመልም ሲቀናው አይቼ ፍጻሜውን ሳላይ በሥራው ቀንቼ ፍሬ የለለው ከንቱ ለካስ ባዶ ኖሯል ግን የእኔው ደስታ ከዓለም ይልቃል (2x) ነፍሴ ተንገድግዳ ልትወድቅ ነበረ ግን ድጋፍ አገኘች ጠላቴም አፈረ የምን መታለል ነው ጉዳቴስ የቱ ነው ተደላድያለሁ ኢየሱስ በቀኝ ነው አረጋግጦልኛል ጌታ እንደማይተወኝ ጠላት ተስፋ ቁረጥ አትችልም ልትጥለኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection