Song Lyrics

ከአቅምህ በላይ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
አዝ፦ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ ለመስራት ከቶ የሚያስቸግርህ ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ በሁለት ዓሣ በአምስት እንጀራ አምስት ሺህ አጠገብክ በበረሃው ስፍራ ዛሬም አይሳንህም ይህንን ልታደርግ የደካከምነውን ጌታ ልትባርክ አዝ፦ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ ለመስራት ከቶ የሚያስቸግርህ ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ ለዕብራውያን መናን ያወረድክ እውር ያበራህ ሸባን በእግሩ ያቆምክ ዛሬም አይሳንህም ይህንን ልታደርግ የዛለውን ጉልበት አድሰህ ልትለቅ አዝ፦ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ ለመስራት ከቶ የሚያስቸግርህ ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ የትኛው ደዌ ለፈውስ አስቸገረህ የትኛው ኃያል ተቋቋመ ያዘህ የኃያላን ኃያል የነገሥታት ንጉሥ ጠላትህን ረሳ መንፈስህን አፍስስ አዝ፦ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ ለመስራት ከቶ የሚያስቸግርህ ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ የሁሉም ዓይኖች ወደ አንተ ናቸው ምስኪኖችህን መተህ ታደጋቸው ነፍሳትን ሁሉ ማዕበሉን አዛዥ በመከራ ጊዜ የጻድቃን አጋዥ አዝ፦ ከአቅምህ በላይ ሆኖ የሚከብድህ ለመስራት ከቶ የሚያስቸግርህ ምን ችግር አለ የሚያዳግትህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ኤልሻዳይ አንተ ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection