በባቢሎን ወንዞች ማዶ አዝነን ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ እጅግ አለቀስን የመጽናናት አምላክ ከላይ ግን ያየናል እንባችንን ጠርጐ ስብራታችንን ይጠግንልናል አዝ፦ ምህረቱ አያልቅምና ለዘለዓለም ቸር ነውና የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጐበኘን መልካሙን መዓዛ በምሥጋና አቅርቡለት በዕልልታ ስገዱለት የችግረኞችን ጩኸት ሰምቶ አይጨክንም ምርጦቹን ኧረ በፍፁም አያስጨንቅም ጠላታቸው ሊበትን በነጐድጓድ አንቀጥቅጦ ረድኤታቸው ከተፍ ይላል ከጸባኦት በግርማው ተገልጦ አዝ፦ ምህረቱ አያልቅምና ለዘለዓለም ቸር ነውና የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጐበኘን መልካሙን መዓዛ በምሥጋና አቅርቡለት በዕልልታ ስገዱለት በሥጋዎቻቸው የገነኑ ፈፅመው ሲወድቁ እግዚአብሔርን በመታመን የሚጠባበቁ በእንባቸው ፍሬ እያሸበርቁ በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ ይገባሉ እንደ ዕንቁ አዝ፦ ምህረቱ አያልቅምና ለዘለዓለም ቸር ነውና የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጐበኘን መልካሙን መዓዛ በምሥጋና አቅርቡለት በዕልልታ ስገዱለት ለእኛ መጠጊያችን ጌታ እግዚአብሔራችን በምንም አንፈራም እርሱ ኃይላችን ከሰይጣን አሰራር ሥሙ ይጠብቀናል ለአሞራም ሳይሰጠን በክንፎቹ አዝሎ ቤቱ ያገባናል አዝ፦ ምህረቱ አያልቅምና ለዘለዓለም ቸር ነውና የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጐበኘን መልካሙን መዓዛ በምሥጋና አቅርቡለት በዕልልታ ስገዱለት (2x)