ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የሚያስፈራም የአንተ ሠራዊት ጠላትን ሁሉ እያሸነፈ በአንተ መሪነት ቀንና ሌሊት ባሕር ተሻግሮ በምድረበዳ ጊንጡን ረጋግጦ ጥቂቱ ሕዝብህ ከአንተ ጋር በዝቶ ርስቱን ጨበጠ ከብዙ በልጦ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) የሰናፍጯን ቅንጣት ቢዘራ ጌታ በምድር እንድትበዛ ያ ጉልበተኛው መጥቶ ረገጣት እንዳትበቅል መስላው ፈዛዛ ግን አልተሳካም አምልጣው ወጣች ሄደች አደገች ጌታ ይመስገን ድንበሯ ሰፋ ለደካከሙት መጠለያ ሆነች አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) ኦ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ እያሸነፈ ዘለዓለም ነዋሪ እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ ከቶ የት አለ ተወዳዳሪ ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን ዘይት የሚቀባ በአደባባዩ በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም እንደ ዘንባባ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x) ኦ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ እያሸነፈ ዘለዓለም ነዋሪ እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ ከቶ የት አለ ተወዳዳሪ ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን ዘይት የሚቀባ በአደባባዩ በቤቱ ተክሎ የሚያለመልም እንደ ዘንባባ አዝ፦ ሕዝብን አበዛህ (2x) የአገሪቱንም ወሰን አሰፋህ የማዳን እጅን ለእኛ ዘረጋህ (2x)