Song Lyrics

ኦ ክብር

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
አዝ፦ ኦ ክብር (4x) ሃሌሉያ ለይሁዳ ነገድ ለሆንከው አንበሳ ለሌለው አምሳያ ልበል ላመሥግነው ከአንጀቴ ውለታው ስለበዛ የመድኃኒቴ በልጅነቴ ጊዜ ያኔ በለጋነት ጠላት ሲጐትተኝ ወደዚያ ባርነት ፀጋው ባይበዛልኝ እጁ ባይደግፈኝ የት ቦታ ነበርኩኝ ክንፉ ባይጋርደኝ አዝ፦ ኦ ክብር (4x) ሃሌሉያ ለይሁዳ ነገድ ለሆንከው አንበሳ ለሌለው አምሳያ ልበል ላመሥግነው ከአንጀቴ ውለታው ስለበዛ የመድኃኒቴ ጥሩር ሆኖልኛል በጦርነት ጊዜ ፍላጻ ሲያቆስለኝ በሃዘን በትካዜ ውለታውን እያሰብኩ ላመሥግነው ጌታን አይገኝምና እንደ እርሱ የሚረዳኝ አዝ፦ ኦ ክብር (4x) ሃሌሉያ ለይሁዳ ነገድ ለሆንከው አንበሳ ለሌለው አምሳያ ልበል ላመሥግነው ከአንጀቴ ውለታው ስለበዛ የመድኃኒቴ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection