Song Lyrics

ድል ለማድረግ ወጣ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
የፈርዖን ገንዘብ ያልማረከው ጀግና ዓይኑ ያልደከመ ያላለቀ ገና ድል ለማድረግ ወጣ በጦርነት ሲቃ በጀርባው አንግቦ የአምላኩን ጦር ዕቃ (2x) የወይኒው አስራት የግርፋት ብዛት አልቻለው ሊያበርደው የፍቅሩን ትኩሳት ፎከረ ያ ጐበዝ ሊጥል ሊገረስስ ጠምዶ በቀኝ እጁ የቃሉን መትረየስ (2x) ገና ዓይኑ ፍጦ ትኩር ብሎ እያየ የጠላትን ምሽግ ቅጥሩን አጋዬ የአርያም እሳት በኃይል ጐብኝቶታል እባቡና ጊንጡን ከእግሩ ስር ረግጦታል (2x) በድካም በረታ ጅማቱ ጠንክሯል አንገብግቦት ፍቅሩ ወኔው ተቀስቅሷል በጀርባው መተልተል ጌታን አከበረ የሞትንም ባሕር በእምነት ተሻገረ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection