Song Lyrics

የዘለዓለም አምላክ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
አዝ፦ የዘለዓለም አምላክ የዘመናት ንጉሥ ሁሉ በሁሉ ነው የናዝሬቱ ኢየሱስ (2x) ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ኢየሱስ አይሰለችም ከቶ አንተ እንኳን ብታምጽ የመስቀሉ ቃል ፈውስ ነው ለሕይወት አምነው ለተጠጉት ይሆናል መሰረት አዝ፦ የዘለዓለም አምላክ የዘመናት ንጉሥ ሁሉ በሁሉ ነው የናዝሬቱ ኢየሱስ (2x) ለሰልፍ አዘጋጅቶ ኃይልን ያስታጥቃል በላይ የቆሙትን ከበታች ይጥላል በትንሳኤው ስልጣን ውጊያውን አካሂዶ ምርኮን ሰብስብ አለው ጠላቱን አሳዶ አዝ፦ የዘለዓለም አምላክ የዘመናት ንጉሥ ሁሉ በሁሉ ነው የናዝሬቱ ኢየሱስ (2x) ፍላጻን ወርውሮ ምሽግን ነደለ በአምላኩ ተማምኖ ውጊያውን ቀጠለ በደም ጐዳና ላይ የኢየሱስ ነው ድሉ ብሎ ዘምሮለት ቆመ በዕጣ ክፍሉ አዝ፦ የዘለዓለም አምላክ የዘመናት ንጉሥ ሁሉ በሁሉ ነው የናዝሬቱ ኢየሱስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection