ገና ህጻን ሳለህ ስጠነቀቅልህ ክንዶችህን ይዤ ዳዴ ሳስተምርህ መራመድን ችለህ ሩጫውን አጠናቅቀህ እንዳልገሰገስክ ዛሬ ግን ታከተህ አዝ፦ ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው በሃሩርር ተቃጥለህ በጥም ተመትተሃል ፍሬህ ሁሉ ደርቆ ፍሬ ቢስ ሆነሃል መንፈሳዊነትህ አሁን ከአንተ ርቆ ለስጋ ተገዛህ ፀጋህ ሁሉ አልቆ አዝ፦ ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው ከግብጽም ጀምሬ እኔ አምላክህ ነህ በደሜ የዋጀሁህ ተው አታሳዝነኝ ምህረት እንደምወድ ጸባዬን ተውቃለህ እልሁን ተውና ታረቀኝ ልጄ ነህ አዝ፦ ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው ምህረት ተነስታለች ልቤ ተናውጣለች እጄ ተዘርግታ ገና ትኖራለች የፍቅር ቀንበሬን ናና ልጫንብህ ጫንቃህንም ስጠኝ ላድንህ . (1) . አዝ፦ ከሸካራው መንገድ እግርህን መልሰው አይበጅህምና ደሜን አትርገጠው ይልቅ እንታረቅ ምህረቴ ብዙ ነው