Song Lyrics

የባዘንከው ውድ ወንድሜ

Pastor Tesfaye Gabisso
Mihiretu Ayalkimina
በከንቱ ሮጠህ ጉልበትህ ባክኖ ጨርሶ አልቆ በኃጢያት ሸክም ነፍሽ መንምና አጥንትህ ደርቆ መድረሻህ ጠፍቶብህ ግራ ተብቶህ የምትባዝን የዓለምን ቤዛ ቀርበህ አማክረው ጌታ ኢየሱስን አዝ፦ የባዘንከው ውድ ወንድሜ አዳምጠኝ እስኪ ልምከርህ ደግሜ ወደ ነፍስህ እረኛና ጠባቂ ና ተመለስ ያለማወቅን ወራት ዘመናት እና ዓመታትን ከኢየሱስ ወዲያ እርካታ ላይገኝ እንዲያው ስታልም በዓለም የሚያንፅ ከቶ አይገኝም ምን ይሻልሃል ድንቁ ኢየሱስን ተቀበለው ያረካሃል አዝ፦ የባዘንከው ውድ ወንድሜ አዳምጠኝ እስኪ ልምከርህ ደግሜ ወደ ነፍስህ እረኛና ጠባቂ ና ተመለስ ዕውቀትን አጥተህ በዚች ዓለም ላይ የተንከራተትክ በጨለማው ደጅ በዲያቢሎስ እጅ የተማረክ ምርኮን . (1) . ከላይ ከሰማይ የወረደው የምስራቹን ትፈልታለህ አማኑኤል ነው አዝ፦ የባዘንከው ውድ ወንድሜ አዳምጠኝ እስኪ ልምከርህ ደግሜ ወደ ነፍስህ እረኛና ጠባቂ ና ተመለስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection