አየሁ (3x) አሻግሬ አየሁ አምነው የሞቱትን ልመስል ተመኘሁ አብርሃምን አየሁ የእግዚአብሔርን ወዳጅ ይስሐቅን ሊሰዋ ለሰይፍ የሚያዘጋጅ ቃሉን ያከበረ ያን ቁም ነገረኛ በሀሳቡም ቁርጠኛ የእምነትን አርበኛ ስውር ጣዖት የለውም ከአምላኩ የሚነጥል በቀውጢ ዘመናት እምነቱን የሚያስቀር ሐዋርያትን አየሁ የጽድቅን ሰልፈኞች የኃጢአትን ጠሮት የእምነትን ቀንድኞች በአንድነት ፀሎት ምድርን ነቀነቋት በብርሃን ወንጌል ባንዴ አጥለቀለቋት ከጌቶቹ ጌታ ፈቃድ ነበራቸው ሥልጣናት አልቻሉም ሊያግዷቸው ሰማዕታትን አየሁ እነ እስጢፋኖስን ዓለም ሲጥላቸው አምነው ኢየሱስን የደም ጥማተኞች ፍዳ ሲያሳዯዋቸው ፊታቸው ሲያበራ ያንሳ ሳይበግራቸው ለዓለም ሲያማልዱ ልክ እንደ ጌታቸው አቤት ሲያስቀና ያ አሟሟታቸው ኮብላዮችን አየሁ በጨለማ ገብተው ሲዖልና ሰይጣን ጌታም የለም ብለው በሥሙ ዘብተው በደሙ ቀልደው የለም ካሉት ጋራ በሞት ተገናኝተው መንፈሴ አያቸው በአንድነት ሲንጫጩ በሙታን ዓለም ውስጥ በጣር ሲወራጩ እንግዲህ ጌታ ሆይ እኔነቴን ግዛ ኪዳኔን አጥፌ ሞትን እንዳልገዛ ብርሃኑ ደብዝዞ ጭጋጉ ሲከበኝ አንተው እየመራህ ወደ ላይ አዝልቀኝ የተፃፈው ሁሉ ለትምህርት ሆኖልኝ በፅናት ታግዬ እንዳሸንፍ እርዳኝ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርት ሆኖልኝ ገድሉን ተጋድዬ እንዳሸንፍ እርዳኝ