Song Lyrics

የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
በሰልፉ ሜዳ በዝቶ ጠላቴ ፍርሃት ሲያርደኝ ፈርቶ ጉልበቴ ጠፍሁ ብዬ ስል ወየው ጌታዬ ከፊቴ አልፏል ኢየሱስ ጋሻዬ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ በዓለም ካለው እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው ጠላት እንደ ንብ ከቦኝ መጣ ምሽጌን ትቼ እኔም አልወጣም በእግዚአብሔር ሥም እሸንፋለሁ ጐልያድም ወድቆ በዓይኔ አየዋለሁ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ በዓለም ካለው እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው ፅኑ ኃያሉ የአምላክ ጦረኛ አንዱ ለሺህ ነው የእምነት አርበኛ ከአመፀኞች እጅ ደሙን በትኖ ፍሬውን ያበዛል በአምላኩ ታምኖ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ በዓለም ካለው እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው ረዳት እንዳለኝ ጠላቴም ያያል እንደ ዘበተ መቼ ይቀራል የመስቀል ፅዋ እኔም ጠጣለሁ ድል ይታወጃል አሻገራለሁ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ በዓለም ካለው እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection