Song Lyrics

እግዚአብሔር መንፈስ ነው

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
እግዚአብሔር መንፈስ ነው በሥጋም አይደፈር እጅግም ታላቅ ነው በሰው የማይገመት ዛሬም እንደቀድሞው ክንዱ ኃያል ያደርጋል ቢወዱም ቢጠሉም ኢየሱስ ይነግሣል አዝ፦ በሰማይ በምድርም ሙሉ ስላጣን ያለው የሚለውጥህ እንጂ የማይለውጥ ነው አልፋ ኦሜጋ ማለት ጌታ ኢየሱስ ነው ሥሙን በመታመን ሲቀርቡት ይቀርባል በደከመች ሕይወት ብርታት ይጨምራል ሞገዱን ፀጥ አድርጐ ሰላምን ይሰጣል ምንጩን አጠጥቶ በረሃን ያለማል አዝ፦ በሰማይ በምድርም ሙሉ ስላጣን ያለው የሚለውጥህ እንጂ የማይለውጥ ነው አልፋ ኦሜጋ ማለት ጌታ ኢየሱስ ነው የማይታየው ባህሪ የዘላለም ኃይሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእውነት ሲያስተውሉ ከጥንትም ጀምሮ ከተሰሩት ደምቆ ይኖራል ኢየሱስ ህልውናው ታውቆ አዝ፦ በሰማይ በምድርም ሙሉ ስላጣን ያለው የሚለውጥህ እንጂ የማይለውጥ ነው አልፋ ኦሜጋ ማለት ጌታ ኢየሱስ ነው የተዓምራት አምላክ ክንዱ መች አጠረ ሰው ያወቀ መስሎት ብዙ የመረመረ ኃጢአትን አጣጥሎ በፍርድ እየኖረ ጌታን የለም ብሎ እጁን አጣመረ አዝ፦ በሰማይ በምድርም ሙሉ ስላጣን ያለው የሚለውጥህ እንጂ የማይለውጥ ነው አልፋ ኦሜጋ ማለት ጌታ ኢየሱስ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection