Song Lyrics

የእኔ ጌታ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
ጌቴ ኢየሱስ የእኔ ቤዛ ጉስቁልናዬ ቢበዛ ከክብሩ ተዋረደልኝ በእኔ ፈንታ ታረደልኝ (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት ኃጢአቴም አስጨንቆት ዝም ብሎ እንደ ጠቦት በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሀል ግብዝ አይደል እንደ ሰው ወረት ጨርሶ ያልነካው በጐልጐታ ላይ የታየው እውነትም እርሱ ፍቅር ነው (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት ኃጢአቴም አስጨንቆት ዝም ብሎ እንደ ጠቦት በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሀል ያጀቡት ሁሉ ፈርጥጠው ለሰይፍ ለጐመድ አጋልጠው በዚያን ምሽት አልቦታል ቃቶ ነፍሴን ታድጓታል (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት ኃጢአቴም አስጨንቆት ዝም ብሎ እንደ ጠቦት በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሀል በግፍ ጀርባው ተላልጦ እግሩንም ለስቃይ ገልጦ ንጹስህ ደሙን ለእኔ ከፍሎ በቀራንዮ ደርቆ ውሎ (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት ኃጢአቴም አስጨንቆት ዝም ብሎ እንደ ጠቦት በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሀል ይህ ፍቅር በሕይወቴ ገብቶ የደህንነት ሥራ ሰርቶ ቆሻሻነቴን ቀይሮ አይቻለሁኝ ውብ ኑሮ (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት ኃጢአቴም አስጨንቆት ዝም ብሎ እንደ ጠቦት በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሀል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection