ትንፋሼንና መንገዴ ሁሉ በእጅህ ይዘህ እንደ ዓይንህ ብሌን አርገህ ለእኔ ተጠንቅቀህ ከሚጐዳኝ ነገር ዘወትር ጋረድክ ሰውረህ ተመሥገን ከማለት ሌላ ለአንተ ምን ልክፈልህ አዝ፦ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘለዓለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ በሀዘን ስመታ ሲከፋኝም አንዳንድ ጊዜ ከብዶ ሲጫጫነኝ ሲደራረብብኝ ትካዜ የመፅናናት ጌታ ማን እንደ አንተ ደረሰልኝ የልቤን ተካፍሎ አይዞህ ሊለኝ ሊያበረታኝ አዝ፦ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘለዓለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ ራሴን አውቀው አለሁ እጅግ አስቀያሚ ነበርኩ ምስኪን አላማ ቢስ በኃጥያት የተቅበዘበዝኩ ግን እንዲያው ወደኸኝ ሰው ሆኛለሁ በአንተ ብርታት በቂ ቃል የለኝም ልገልፅ የውለታህን ብዛት አዝ፦ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘለዓለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ አህዛብ ባያውቁህ የእኔ ነፍስ ታውቅሃለች የፍቅር ፊትህን በእየለት ትናፍቃለች ያለ አባትነትህ መኖር ከቶ አይሆንላትም መሳይ አጭበርባሪ ሁሉ ከአንተ አይነጥላትም አዝ፦ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘለዓለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ (2x)