አዝ፦ ተመሥገን ጌታዬ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (2x) በጉለት እንዲቆይ ሳይደክም ጉልበቴ ኃይልን አስታጠቀኝ ከላይ መድኃኒቴ በብዙ ውሽንፍር ቢያጥለቀልቅ ጐርፉ ጠላቶች በአንተ ሥም ሁሉም ተሸነፉ አዝ፦ ተመሥገን ጌታዬ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (2x) የኑሮዬ ተገን ክብሬ መከታዬ ኃይሌም ይታደሳል አንተ ነህ ተድላዬ ማዕበሉ ተነስቶ ሊያሰጥመኝ ሲቃጣ በገሀድ አያለሁ ረዳቴ ስትመጣ አዝ፦ ተመሥገን ጌታዬ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (2x) የእግዚአብሔር ቸርነት አያልቅም ቢቆጠር ነነዌም ብትሰራ ኃጢአት በማግበስበስ አምላክም አስቦ እነርሱን ለመምከር አዘዘው ዮናስን ለሕዝቡ እንዲናገር አዝ፦ ተመሥገን ጌታዬ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (2x)