Song Lyrics

ተጠፍሬ ያየኸኝ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
በጉልበቴ ያለሁ ገና ያልተነካሁኝ በመንገድ አጠገብ በውጭ የታሰርኩኝ ነጻነት የሌለኝ ውርንጫ ነበርኩኝ ሳላውቅህ አውቀኸኝ አንተ ግን ፈታኸኝ አዝ፦ ተጠፍሬ ያየኝ ያለ ውዴታዬ ነጻነት የሰጠኝ ወዳጅ አለኝታዬ ማነው ከአንተ በቀር ባለ ውለታዬ ሌላ ምን እላለሁ ተመሥገን ጌታዬ (2x) በዚህ በጉልበቴ ለአንተ ክብር ሮጬ እባብና ጊንጡን በሥምህ ረግጬ መሸለሜን ሰምቶ ጠላት አኮረፈ አንተን በላዬ ሲያይ ጥላው ተገፈፈ አዝ፦ ተጠፍሬ ያየኝ ያለ ውዴታዬ ነጻነት የሰጠኝ ወዳጅ አለኝታዬ ማነው ከአንተ በቀር ባለ ውለታዬ ሌላ ምን እላለሁ ተመሥገን ጌታዬ (2x) ከእሥራት ፈተኸኝ በእኔ ልትቀመጥ ይህን ታላቅ ዕድል ለምስኪኑ ልትሰጥ ለመሆኑ እኔ ኧረ እኔ ማን ነኝ ይገባኛል እንዴ ለዚህ ልትመርጠኝ አዝ፦ ተጠፍሬ ያየኝ ያለ ውዴታዬ ነጻነት የሰጠኝ ወዳጅ አለኝታዬ ማነው ከአንተ በቀር ባለ ውለታዬ ሌላ ምን እላለሁ ተመሥገን ጌታዬ (2x) ሆሳዕና በአርያም እያሉ ቢጮሁ ልብሳቸውንና ቅጠል ቢያነጥፉ የኔ እግር ቢረግጠው አንተ በላዬ ነህ ክብሩ የራስህ ነው ኑር ዘለዓለም ከብረህ ውርጭላው ተፈትቶ የክበር ዕቃ ሆኗል ነጻነትን ሰጥቶት ጌታው ከብሮበታል የተፈታውን ሳይሆን የፈታውን አክብሩ ሆሳዕና በሉ መንገሡንም አውሩ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection