Song Lyrics

በአምላክ አምሳል

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
በአምላክ አምሳል ተፈጥሬ በጐ ለማድረግ በፊቱ ስኖር ሳለሁ ኃጥያቴ አድርጐኝ ነበር ከንቱ ክቡር ሆኜ ሳለሁ አምላኬን ረስቼ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰልኩ እኔ ሳልፈልገው ጌታ ሊፈልገኝ ከላይ መጥቶ ከእርኩሰት ውስጥ ነጥቆ አወጣኝ በዓለም ላይ ተንከራቶ ሸክሜን ወሰደልኝ በሥጋዬ ሞተልኝ የማይቆጠረውን በደሌን ፋቀልኝ መድኃኒቴ ነው ኢየሱሴ ጌታዬና አምላኬ ስለ መልካሙ ውለታው ላመስግነው ተንበርክኬ ምህረቱ ብዙ ነው ማዳኑ ግሩም ነው ለአምላካዊ ፍቅሩ መጨረሻ የለው በሞት ጥላ ውስጥ እያለሁ በድቅድቅ ጨለማ ኢየሱስ ብርሃኔ መጥቶ አዳነኝ መሀሪ ነውና ለፍርድ የተመደብኩ ለሲዖል የታጨሁ የቁጣ ልጅ ስሆን ከፍጥረቴ ቅጣቴን ውስዶ ያ ረድኤቴ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection