የሠራዊት ጌታ ኃያሉ መድህኔ ሲጠብቀኝ ሳለ ፍርድና ኩነኔ በኃጢአት ጣር ስኖር ተሳስሬ ከእስራቴ ፈታኝ መራኝ ወደ አገሬ (2x) አዝ፦ በጭንቄ ተጨንቆ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ላረባሁት ልጁ እንዲያ ተጐሳቁሎ ደሙን አፈሰሰ በፍቅሩ ተገዶ ሕይወቴን አዳናት ስለ እኔ ተዋርዶ (2x) ፍፁም የማልረባ ማስተዋል የሌለኝ አዳኜን የማላውቅ ፍርድ የሚጠብቀኝ የሰይጣን ምርኮኛ ሸክም የተጫነኝ እንዲህ ያለሁ ነበር ጌታ ሳያገኘኝ (2x) አዝ፦ በጭንቄ ተጨንቆ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ላረባሁት ልጁ እንዲያ ተጐሳቁሎ ደሙን አፈሰሰ በፍቅሩ ተገዶ ሕይወቴን አዳናት ስለ እኔ ተዋርዶ (2x) ፍርሃት መጠራጠር ክፋትና እርኩሰት ይወገድ ትዕቢት ቅናት ምቀኝነት ተንኮልና ውሸት ሀሜት ክፉ ምኞት ተደምስሰው ይጥፉ በጽዮኑ አለት (2x) ይውደቁ ይፈጩ ይድቀቁ በአንድነት ቀንበሩ ተሰብሯል ይቅርብኝ ባርነት ዕዳዬም ተከፍሎ ታውጇል አርነት ሞትም አያስፈራኝ ተሰጥቶኛል ሕይወት (2x)