Song Lyrics

እንዲህ አልነበርኩም

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
አዝ፦ እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x) ሥምህን እንደዋዛ ተሽክሜዋለሁ ክርስቲያን ተብዬም ይኸው እጠራለሁ ውስጤ ቢመረመር ግን እንዲህ አይደለም የመንፈስ ፍሬ ከቶ በእኔ የለም አዝ፦ እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x) የለየልኝም ከሃዲ አልሆንኩኝም ክርስቲያንም ሆኜ አልበረታሁም እንዲያው ለብ ብዬ አስቸግሬያለሁኝ ዛሬስ በንስሃ ተደፍቻለሁኝ አዝ፦ እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x) ለክርስቲያኖች ለአንተ ያለኝ ፍቅር ላገልግልህም ሥምህን ላስከብር የነበረኝ ፀሎት ያ ሁሉ ትጋቴ እፍገመገማለሁ ከድቶኛል ብርታቴ አዝ፦ እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x) ሽቅብ እንደመውጣት ቁልቁለት ሄጃለሁ ወደ ሞትም ደጃፍ በጣም ቀርቤያለሁ አሁንም በቃልህ ተገስጫለሁኝ ዳግም አንሳኝ ብዬ ተማጽኛለሁኝ አዝ፦ እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection