ኃጢአት በዛብኝ ጉልበቴም ደከመ መራመድ አልቻልኩም መንገዴም ጨለመ ጠላቴም ይህን ሲያይ ሊሰብረኝ አለመ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ መጥተህ አውጣኝ አንተን እያሳዘንኩ ደምህን እየረገምኩ ለልጆችህ ደግሞ እንቅፋት እየሆንኩ መላው ጠፋኝ ጌታ ግራ ተጋባሁኝ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ መጥተህ አውጣኝ ቃልህን እንዳላነብ ፍላጐቴ ከድቶኝ ደግሞም እንዳልፀልይ ድካም ተጫጭኖኝ በጣሙን ዝያለሁ ተጐሳቁያለሁ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ መጥተህ አውጣኝ በቅዱስ መንፈስህ ሕይወቴ ታትሞ በልጆችህ መሃል የእኔ መኖር ጠቅሞ ልገናኝህ አብቃኝ ሁሉ ተፈጽሞ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ መጥተህ አውጣኝ መውደቅ በጥቂቱ መሞት በጥቂቱ መሆኑን አይቻለሁ ከመውደቅ ጠብቀኝ ማዕበሉ እንዳይጥለኝ ጐርፉም እንዳይወስደኝ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ መጥተህ አውጣኝ