የፀጋ የምህረት ዘመኑ አብቅቶ ብርሃን ተሰውሮ የጥሪው ቀን መሽቶ ሰማያት ተፈተው ምድር ሳትናውጥ በነበልባል እሳት ጌታም ሳይገለጥ አዝ፦ አስብበት ዛሬ ነገን አትጠብቅ ራስህን ስትደልል ዘመንህም አይለቅ ሕይወት ኢየሱስ ነው ሌላስ አታገኝም አምነህ ድነህበት ታተም ለዘለዓለም አብሮ ደስ ይበለን ትንሽ ቆይ ስትልህ ዓለም በለዘብታ እያባበለችህ ተደላ ትካዜና ቁጭትን ጠብቆ ሲዖል እንዳትገባ ሳታስበው ከቶ አዝ፦ አስብበት ዛሬ ነገን አትጠብቅ ራስህን ስትደልል ዘመንህም አይለቅ ሕይወት ኢየሱስ ነው ሌላስ አታገኝም አምነህ ድነህበት ታተም ለዘለዓለም የእግዚአብሔር ነገር ለፍጥረታዊ ሰው ሊገባው አይችልም ፍፁም ሞኝነት ነው ፍጥረታዊውን ሥጋ መንፈሱ ሲሽረው ያኔ ትረዳለህ መንገዱ ጥበብ ነው አዝ፦ አስብበት ዛሬ ነገን አትጠብቅ ራስህን ስትደልል ዘመንህም አይለቅ ሕይወት ኢየሱስ ነው ሌላስ አታገኝም አምነህ ድነህበት ታተም ለዘለዓለም በመንታ መንገድ ላይ ሆነህ ስታማርጥ ፈጽሞ ላትረካ መንገድ ስትለዋውጥ ሞት ጥላውን ጥሎ አፍኖ ሳይወስድህ ጌታን ተቀበለው እርሱ ነው የሚያረካህ አዝ፦ አስብበት ዛሬ ነገን አትጠብቅ ራስህን ስትደልል ዘመንህም አይለቅ ሕይወት ኢየሱስ ነው ሌላስ አታገኝም አምነህ ድነህበት ታተም ለዘለዓለም