Song Lyrics

ሕይወት ለተጠሙ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Menfes New
ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ ቀርበው ለማነጽ የሚጠቅም የፀጋ ቃል ይዘው አፋቸውን ሲከፍቱ በክርስቲያን ቋንቋ ምንኛ ደስ ይላል ሲቀር አሉባልታ አዝ፦ ሕይወት ለተጠማ የምሥራች በሉ እንዲህ ያለ ኑሮ ወደው ቢቀበሉ ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ይሰበካል የሚያረካ ምንጭ ለሁሉም ተሰብኳል የመንፈስን ፍሬ አዝሎ በሕይወቱ የአምላክን ደራሲ አውቆ ማንነቱን ጌታን ሲያንፀባርቅ እስከ ዕለተ ሞቱ ከክበር ወደ ክብር ይለወጣል ቤቱ አዝ፦ ሕይወት ለተጠማ የምሥራች በሉ እንዲህ ያለ ኑሮ ወደው ቢቀበሉ ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ይሰበካል የሚያረካ ምንጭ ለሁሉም ተሰብኳል ሸክምን ለማራገፍ በመስቀሉ እግር ክርስቲያን ሲንበረከክ ልቡ ሲሰባበር ሚስጥሩን ለጌታ በእንባ አወያይቶ ተፅናንቶ ይነሳል በእምነት ተሞልቶ አዝ፦ ሕይወት ለተጠማ የምሥራች በሉ እንዲህ ያለ ኑሮ ወደው ቢቀበሉ ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ይሰበካል የሚያረካ ምንጭ ለሁሉም ተሰብኳል ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረቱ ጠንክሮ ሕይወት ሲስተካከል ግንኙነት ሰምሮ ኑሮ ከኢየሱስ ጋር ዓለምን ያስንቃል ለዛ አለው ይጥማል ቢመረጥ ይበጃል አዝ፦ ሕይወት ለተጠማ የምሥራች በሉ እንዲህ ያለ ኑሮ ወደው ቢቀበሉ ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ይሰበካል የሚያረካ ምንጭ ለሁሉም ተሰብኳል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection