Song Lyrics

እምቢ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
የሙታን ባልንጀራ ኃጢአተኛ ሳለሁ ጌታን በማመኔ ከክፋት ድኛለሁ ግን ሕይወቴን እንድክድ አሁን ብከተልም ኢየሱሴን ክጄ ግኡዝ አላመልክም አዝ፦ እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል እቶኑ ይታየኛል ግለቱ ይሰማኛል ፈርቼ አልጠላውም አንስቶ ያጠራኛል ለሰማያዊው መንግሥት ብቁ ያደርገኛል ሰው እንደሚያስበው መቼ ይጐዳኛል አዝ፦ እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል በእሳት ውስጥ ያሉትን ጭሱ ሳይነካቸው አስረው የጣሏቸው ወላፈን ፈጃቸው እንደዚህ የሚሰራ ኃያል ጌታ ካለኝ ሰባት እጥፍ ያንድድ እኔ ምን ቸገረኝ አዝ፦ እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል እምቢ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection