Song Lyrics

እታገላለሁ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ ጉልበቴን አጠንክሬ ክንዶቼን አበርትቼ እጓዛለሁ በደስታ ሳይከፋኝ ተፅናንቼ አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ የሰላምን ወንጌል በእግሬ ተጫምቼ በክንፉ ተማምኜ በደሙም ተሸፍኜ አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ ፍላጻ የማይበሳውን ጥሩሩን እልብሳለሁ ሕይወቴን ላላስድፍር በተጠንቀቅ ቆማለሁ አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ እምነት ጋሻቸው ሆኖ ቅዱሳን ከተጓዙ ኑሯቸው ከተቃና ድልን ከተቀዳጁ አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ በመታገል ከሆነ ማሸነፍ ድል መንሳት ከዚህ ዓለም ገዢ ጋራ ከክፋትም ሠራዊት አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ የተዘጋጀልኝን ከኢየሱስ ከጌታዬ እወስዳለሁ አክሊሌን በሚገባ ታግዬ አዝ፦ እታገላለሁ እታገላለሁ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection