Song Lyrics

የማይናወጥ መሰረቴ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
አዝ፦ የማይናወጥ መሠረቴ ጌታ ኢየሱስ መከታዬ የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ በዚያ ሸለቆ በአዘንቱ ቦታ ኢየሱስ አልተውከኝም ደጋፊ እንዳላጣ ሕይወቴ ነህና ተድላ መከታዬ ኢየሱስ ከአንተ በቀር የቱ ነው ጋሻዬ አዝ፦ የማይናወጥ መሠረቴ ጌታ ኢየሱስ መከታዬ የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ የዓለሙ ወጀብ ሊመታኝ ሲቃጣ ጌታ አለቀቀኝም ከእጁ እንድወጣ ወደ እርሱ የመጡትን ልጆቹን ያፈቅራል በእቅፍ ውስጥ ይዞ ይጠብቃቸዋል አዝ፦ የማይናወጥ መሠረቴ ጌታ ኢየሱስ መከታዬ የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ የጣርህን መጠን በምን ልገምተው የውለታህን ልክ በምን ላስተውለው ከቶ እንዳልዘነጋው ያንን መስቀልህን ደግሞም እንዳልረሳ ለእኔ ማንባትህን አዝ፦ የማይናወጥ መሠረቴ ጌታ ኢየሱስ መከታዬ የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection