አዝ፦ እግዚአብሔር ኃያል በሰልፉም ደግሞ ኃያል ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x) ህዝቡን ከልሎ የሚዋጋ ለጠላት ዛቻ የማይሰጋ ብድራትን መላሽ የእኛ አምላክ ይርታ እንጂ መረታትን አያውቅ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ኃያል በሰልፉም ደግሞ ኃያል ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x) የእምነት ባለድል ሳይጸጸት ጌታን አምኖ ሰው አያፍርበት ለተስፋው ፈቶ ሰንሰለት ሕይወቱን ሰጥቷል ሳትሰስት (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ኃያል በሰልፉም ደግሞ ኃያል ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x) አንተም በኃይሉ ድል ነስተህ በእቶን ተፈትነህ ነጥረህ ለመንግሥቱ ብቁ ሆነህ እንድትወጣ ጌታ ይርዳህ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ኃያል በሰልፉም ደግሞ ኃያል ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x) ያን ጊዜ ተዋግቶ የረታ የጠላቱን ጅማት የፈታ በፅኑ አመታት የሚመታ ሁሉን የሚችል የድል ጌታ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ኃያል በሰልፉም ደግሞ ኃያል ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x)