አዝ፦ ምሥጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x) የአመጽ ፈሳሽ ሲያስፈራራኝ የሲዖል ጣርም ሲከበኝ አምላክህ የታለ ሲለኝ ባላኝጣዬ ሲያፌዝብኝ ከመሠረቴ ሊነቅለኝ ቆይ ብቻ ሲል ሲዝትብኝ የጌታን ሥም እጠራለሁ ከጠላቴም አድናለሁ አዝ፦ ምሥጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x) የጌታ ኢየሱስ ሥም ለእኔ የፀና ግንብ ነውና እስከዛሬም እርሱን ጠርቶ ማንም አላፈረምና በኪሩቤል የሚኖረው ሙሉ ተስፋ ስለሰጠኝ ታምኜ ሥሙን እጠራለሁ ከጠላቴም እድናለሁ አዝ፦ ምሥጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x) በጨነቀኝ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔርን ጠራሁት ስቅስቅ እያልኩኝ በእንባ የሆዴን ብሶት ነገርኩት ከዚያም በበቀል ወረደ ከሰማይ አንጐደጐደ በመብረቁ አወካቸው በፍላጻው በተናቸው አዝ፦ ምሥጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x) ለጥርሶቻቸው ንክሻ አላደረገኝምና ከተዘረጋብኝ ወጥመድ ሁሌ አድኖኛልና አርነቴን ከሚቀማ ከሰይጣን ጋርዶኛልና ሥሙ ይክበር ሃሌሉያ እያልኩኝ ልኑር በእርሱ ጉያ አዝ፦ ምሥጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ (2x)