Song Lyrics

ዝም ብዬ እቆማለሁ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
በዚች ምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አለብኝ አኔ ዝም እላለሁ አንተ ተዋጋልኝ አንተን ያሰለፉ ስልፉ ሰምሮላቸው አይቼ ተምሬያለሁ ከድል ዝማሬያቸው አዝ፦ ዝም ብዬ እቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ ለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (2x) ሰልፉ የእኔ መስሎኝ እረታለሁ ብዬ በሥጋዬ ስታገል ተዝለፍልፌ ዝዬ መረታቴ ነው እኮ ኢየሱስ ጌታዬ ኧረ ቶሎ ናልኝ አይብዛ መከራዬ አዝ፦ ዝም ብዬ እቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ ለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (2x) የእሳት ሰረገላው መለኮታዊው ጦር የድምፅህ ነጐድጓድ ጠላት የሚያሸብር ይምጣ ይዋጋልኝ እኔ ኃይል የለኝም አሁን አውቄያለሁ ሰልፉ የእኔ አይደለም አዝ፦ ዝም ብዬ እቆማለሁ ሰልፉን ለአንተ ለቃለሁ በእምነት ወደ አንተ አያለሁ ጌታ ሆይ ድልህን እጠብቃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection