የጠላቴን እራስ ቀጥቅጠህ ከመጋጋው እኔን ነጥቀህ ቅዱስ ደምህን አፍስሰህ ለሙት ልጅህ ሕይወት ሰጥተህ ታላቁን ኪዳን ድኛለሁ አሁንም መስማት አሻለሁ አዝ፦ በጊዜውም አለጊዜውም ትዕግሥትህን ፀንቼ ቆሜ ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ ስቅበዘበዝ መክረኸኛል ስተክዝ አፅናንተኸኛል ባቆስልህም ወደኸኛል ዘወትር ተሸክመኸኛል እስከዛሬ ችለኸኛል ቅዱስ ሥምህ አቁሞኛል አዝ፦ በጊዜውም አለጊዜውም ትዕግሥትህን ፀንቼ ቆሜ ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ ዘወትር በሁሉም ስፍራ አንተን ልምሰል አንተን ልፍራ ከዓለም አድርገኝ ልዩ በእኔም ሕይወት አንተን ይዩ ሥጋዬን ለዓለም ሰቅዬ ልጓዝ አንተን ተከትዬ አዝ፦ በጊዜውም አለጊዜውም ትዕግሥትህን ፀንቼ ቆሜ ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ በድካም ሕይወቴ ላልቶ አካሄዴም ተበላሽቶ ቅዱስ ሥምህ አንዳይሰደብ አደራ ልጅህን አስብ እስክትመጣልኝ በክብር አንተን አስከብሬ ልኑር አዝ፦ በጊዜውም አለጊዜውም ትዕግሥትህን ፀንቼ ቆሜ ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ በከፍታም በዝቅታም በሀዘንም በደስታም ሳልደናገር በእርጋታ በፈተናም ሳልረታ በትጋት ፀንቼ በእምነት ፊትህን ልየው በክበር አዝ፦ በጊዜውም አለጊዜውም ትዕግሥትህን ፀንቼ ቆሜ ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ