አዝ፦ ልጅነቴ አላለቀም ነኝና ብላቴና ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (2x) በግብዝነት ተሯሩጬም ከእውነትህም ተሳሰቼ በስሜትህ ተገፋፍቼ የቃልህን ሙላት አጥቼ እንዳልጠፋ በጠላት ተጠቅቼ አዝ፦ ልጅነቴ አላለቀም ነኝና ብላቴና ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (2x) ለጋነቴ እኔን አጋልጦኝ መከራውም አጠውልጐኝ አውሎ ነፋስ አስገምግሞኝ የአሸዋው መሠረት አዝሞኝ ክፉኛ ገፍትሮ እንዳይጥለኝ አዝ፦ ልጅነቴ አላለቀም ነኝና ብላቴና ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (2x) ወተት ብቻ መጋቱን ተቼም አጥንቱንም ደግሞ በልቼ እንደ ህጻን ማሰቤ ቀርቶ በጐልማሳነት ተተክቶ ላይ እሻለሁ ሕይወቴ ተገንብቶ አዝ፦ ልጅነቴ አላለቀም ነኝና ብላቴና ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (2x)