Song Lyrics

ተመለስ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
ተስፋህ ጨልሞ ጭንቀት አስጥሞህ መጥፋትህ ታይቶኝ ከዚያ ጣር ወጥቼ ደስ ብሎህ ነበር አግኝተህ እፎይታ ለምን ነው ዛሬስ የሆንከው ከርታታ አዝ፦ ተመለስ (3x) ልጄ ሆይ (2x) በእኔ ተማምነህ ስትመላለስ በእንባ በፀሎት ቀርበህ ስትታደስ የነበረህ ወዝ መልክህስ የታለ ናና ታረቀኝ ፀጋዬ እያለ አዝ፦ ተመለስ (3x) ልጄ ሆይ (2x) የፍቅር ወንጌል ለሌላው ሰብከህ ሸክማቸው ከብዶህ ለጠፉት አልቅሰህ መስክረህ ወደ ሕይወት አምጥተህ ሳይህ አዝናለሁ አንተ ግን ኮብልለህ አዝ፦ ተመለስ (3x) ልጄ ሆይ (2x) ቤቴ ናፍቆህ ብትመለስልኝ ይቅርታ ፈልገህ ብትመጣልኝ የምህረት እጄስ ተዘርግታለች የፍቅር እንባም ዓይኔ ታፈሳለች አዝ፦ ተመለስ (3x) ልጄ ሆይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection