Song Lyrics

የባዘነውን ፈላጊ አምላክ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
የጠራውን መስሎ መኖር መጋደሉን ፈርቶ የገባለትን ጣለና ተስፋውን ዘንግቶ የሙት ልጅ የነበረ ሰው ከጥፋት የዳነ የተሰዋለትን ኢየሱስ ያንን አዳኙን ከዳ አዝ፦ የባዘነውን ፋላጊ አምላክ የምህረት አምባ ለጠፉትም የምታነባ ከሕይወት ወደ ሞት ከእረፍት ወደ ጭንቀት የሄደውን መልስ እባክህ ጌታ ወደ መንጋህ በረት ተዋግቶ የማረከውን ያንን ስመ ጥሩ ጀግና ጌታውን ሊያስከብር ቆርጦ ተሰልፏልና ጠላት ከባሻገር ቆሞ ቅናት እያጋየው እሸክላውን ዘርግቶበት ወንድሜን ዘለፈው አዝ፦ የባዘነውን ፋላጊ አምላክ የምህረት አምባ ለጠፉትም የምታነባ ከሕይወት ወደ ሞት ከእረፍት ወደ ጭንቀት የሄደውን መልስ እባክህ ጌታ ወደ መንጋህ በረት በአምላኩ መቅደስ ውስጥ ሆኖ ተማምኖ እያገሳ ገናናነቱንም ሲያውጅ የይሁዳን አንበሳ እንግዳ ነገር ወሰደ ነዝንዞ ጨቅጭቆ ፀጋ ክብሩን አስላጭቶ እጅግ አስጨንቆ አዝ፦ የባዘነውን ፋላጊ አምላክ የምህረት አምባ ለጠፉትም የምታነባ ከሕይወት ወደ ሞት ከእረፍት ወደ ጭንቀት የሄደውን መልስ እባክህ ጌታ ወደ መንጋህ በረት ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ ጉልበቱን ከርክሮ ዜናውን እየተረከብን በህመም አደንዝዞ ያ የክህደት አውሎ በሕይወቱ ነፍቶበት ከወይኑ ግንድ ገነጠለው ፍሬ እንዳይገኝበት አዝ፦ የባዘነውን ፋላጊ አምላክ የምህረት አምባ ለጠፉትም የምታነባ ከሕይወት ወደ ሞት ከእረፍት ወደ ጭንቀት የሄደውን መልስ እባክህ ጌታ ወደ መንጋህ በረት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection