Song Lyrics

እንባዬን አይተህ ጌታ

Pastor Tesfaye Gabisso
Egziabher Hayal
አንድን ነገር ሽቼ ደጅ ጠናለሁኝ ፈቃድህ ከሆነ በዓይንህ ተመልከተኝ ያቺን ብሩክ እጅህን ዘርጋብኝ አዝ፦ እንባዬን አይተህ ጌታ ለቅሶዬን ሰምተህ ጌታ መሻቴን ስጠኝና ኢየሱስ ላመስግንህ (2x) አንተን ተስፋ አድርጌ በቃልህ ፀንቼ መልሴን አጠብቃለሁ በተመስጦ ሆኜ ታማኝነትህን ተማምኜ አዝ፦ እንባዬን አይተህ ጌታ ለቅሶዬን ሰምተህ ጌታ መሻቴን ስጠኝና ኢየሱስ ላመስግንህ (2x) በጐ ስጦታና ፍፁም በረከት ሁሉ ከብርሃናት አባት ከላይ ይወርዳሉ ከዙፋንህ ይንቆረቆራሉ አዝ፦ እንባዬን አይተህ ጌታ ለቅሶዬን ሰምተህ ጌታ መሻቴን ስጠኝና ኢየሱስ ላመስግንህ (2x) መራራነቴ ያብቃ እሾህነቴም ያብቃ መፈራረሴም ያብቃ በአንተ ፀጋ ልገንባ ጐስቋላነቴን ጌታ ሆይ እንካ አዝ፦ እንባዬን አይተህ ጌታ ለቅሶዬን ሰምተህ ጌታ መሻቴን ስጠኝና ኢየሱስ ላመስግንህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection