አዝ፦ ኃጢአት ሥሩን ሰዶ ሳይጠነክርብኝ ሳይታወቀኝ አድጐ ሞትን ሳይወልድብኝ ንስሃ እንደገባ በጊዜ ገስፀኝ (2x) የሌብነት ካባ ወርቁም ሆነ ብሩ ከድንኳኔ በታች ተቀብረው ላይቀሩ ቃልህን ለመጠበቅ ልጆችህ ሲጥሩ በተደበቀ እርም ወድቀው ሲማረሩ አዝ፦ ኃጢአት ሥሩን ሰዶ ሳይጠነክርብኝ ሳይታወቀኝ አድጐ ሞትን ሳይወልድብኝ ንስሃ እንደገባ በጊዜ ገስፀኝ (2x) ኃጢአትን ታቅፌ ጌታ ሆይ ብልህም ውስጤ ሳይስተካከል ብዘምርልህም ወይም ብሰብክልህ ጉድለቴን ሳላውቀው ምን ፍሬ ይገኛል በከንቱ መሮጥ ነው አዝ፦ ኃጢአት ሥሩን ሰዶ ሳይጠነክርብኝ ሳይታወቀኝ አድጐ ሞትን ሳይወልድብኝ ንስሃ እንደገባ በጊዜ ገስፀኝ (2x) ጌታ ሆይ የለኝም ከአንተ የምቀርበው ድካሜን ብርታቴን ተረድቶ የሚያውቅልኝ ስለዚህ መርምረህ ንገረኝ በደሌን ንስሃ ልግባ እኔ አዋርጄ እራሴን አዝ፦ ኃጢአት ሥሩን ሰዶ ሳይጠነክርብኝ ሳይታወቀኝ አድጐ ሞትን ሳይወልድብኝ ንስሃ እንደገባ በጊዜ ገስፀኝ (2x)